ውይይቱ የኤጀንሲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የየቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመራሮች በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን፣ የ2013 ዓ.ም አፈጻፀም እና የ2014 ዓ.ም ዕቅድ በኤጀንሲው የዕቅድ እና ሪፖርት አገልግሎት በሠፊው እንዲቀርብ ተደርጎ በተሳታፊዎች አጠቃላይ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ 

ውይይቱ በንግግር የከፈተቱት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ባለፈው የበጀት ዓመት ከተገኙ አንኳር ውጤቶች መካከል፡-

  • የኮቪድ 19ን ተፅዕኖ መቋቋም
  • እንደ ሃገር በትግራይ ክልል በተከሰተው ሁኔታ ከኤርትራ ስደተኞች ጋር ተያይዞ ያጋጠሙ ችግሮችን በተሻለ ሁኔታ መምራት መቻሉ
  • በተመላሾች ፕሮጀክት ጽ/ቤት በኩል የተፋጠነ የተመላሽ ቅበላ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ለተመለሱ ዜጎች ሠፊ ድጋፍ መደረጉ
  • በነበሩ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ከ20 ሽህ በላይ ስደተኞችን መርምረን መቀበል መቻላችን
  • የተሻለ ተደራሽነት (visibility) እና የገጽታ ግንባታ ሥራዎች መከናወናቸው

ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ፡-

  • የቴክኖሎጂ ዝማኔ (Digitalization)
  • ብቁ እና ውጤታማ አፈጻፀም (Efficiency and Effectiveness)
  • የአቅም ግንባታ (Capacity Building)
  • የአሠራር ሥርዓት ማዕቀፍን ማጠናከር (Strengthening Standard Working Procedures)
  • አጋር አካላትን ማስፋት (Expanding Partners Base)

መሆናቸውን ተጠቃሽ መሆናቸውንና እነዚህንም ለማሳካት የተሻለ የኮሚኒኬሽን ሥራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በኤጀንሲው የሰው ሃብት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት በኩል የለውጥ ሥራ አመራርን የተመለከተ መነሻ ሃሳብ ለተሳታፊዎች ቀርቦ አጠቃላይ በተነሱ ጥያቄዎች በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ማጠቃለያ እንዲሁም ቀጣይ የአፈፃፀም አቅጣጫ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡