የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ አመራሮች እና ሰራተኞች የሃገር መከላከያ ሰራዊትን “ሀገርን የማዳን ዘመቻ” ለመደገፍ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ብር 11,333,741.96 (አስራ አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሽህ ሰባት መቶ አርባ አንድ ከዘጠና ድስት ሳንቲም) ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረክበዋል።

በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኤጀንሲያችን ዋና ዳይሬክተር መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም አመራሩና ሰራተኛው ከጎረቤት እና ሌሎች አገሮች ተሰደው የመጡ ስደተኞችን ጥበቃ እና ድጋፍ የሚያደርጉ በመሆናቸው የጦርነትና የግጭትን ተፅዕኖ ለመፍታት የሚሰሩ በመሆኑ ነው የሃገርን አንድነት ለማስቀጠልና ህልውናን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለውን የመከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ በቁርጠኝነት የተነሱት ብለዋል።

የኤጀንሲው አመራርና ሰራተኞች ከአንድ ወር ደመወዝም በተጨማሪ ለብሄራዊ የደም ባንክ ለሁለተኛ ጊዜ  የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናውነዋል።

የኤጀንሲው አመራሮችና ሰራተኞች ለዜጎች ሲቀርቡ ለነበሩ አገራዊ ጥሪዎች ምላሽ ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በተደረገው ጥሪ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።